Uncategorized

ቴዲ አፍሮ ኢትዮጵያዊውን ወጣት በ700 ሺህ ብር ከሞት አተረፈ

ከሶስት ዓመታት በፊት  መቀሌ የሚገኙትን ቤተሰቦቹን ተሰናብቶ ኑሮውን ለማሸነፍ ለስራ ወደ ፑንትላንድ ያመራው ኢትዮጵያዊው የ31 ዓመት ወጣት አስመሮም ኃይለስላሴ ፑንትላንድ ውስጥ ሆቴል ከፍቶ እየሰራ ነበር፡፡

ከባለቤቱና ከአንዲት ሴት ልጁ ጋር አንድ አመት ያህል እንደቆየም ታህሣስ 2002 ዓ.ም አምስት የታጠቁ ሶማሊያውያን በሌሊት ለዝርፊያ ባለቤቱን ለመድፈርና ግድያ ለመፈፀም ግብ ግብ ይገጥሙታል፡፡ በወቅቱም አብረውት ከነበሩት ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን ራሳቸውን ለመከላከል በወሰዱት እርምጃ ከዘራፊዎቹ አንዱ ህይወቱ ያልፋል፡፡ አብረውት የነበሩት ኢትዮጵያውያን አምልጠው ወደ ሀገራቸው ይመለሳሉ፡፡ አስመሮም ግን ታስሮ ጉዳዩን ሲከታተል ይቆያል፡፡

ቤተሰቦቹ እንደሚሉትም በአካባቢው የሚኖሩ ሶማሊያዊያን አስመሮም ጥፋት እንደሌለበትና በሰዓቱም ተኝቶ እንደነበር ምስክርነታቸውን ሰጥተውለታል፡፡ ሆኖም ምስክርነታቸው ተቀባይነት ባለማግኘቱ ከአንድ አመት እስር በኋላ በሞት እንዲቀጣ ተወሰነበት፡፡

አስመሮም በእስር ቤት ሳለ ሚስት በግብግቡ ወቅት ጉዳት የደረሰባትን የሰባት አመት ሴት ልጇን ይዛ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሰች ሲሆን ታዳጊዋ ላይ የደረሰው ጉዳት ከፍተኛ ስለነበር ህይወቷ አልፏል፡፡

የልጇ መሞት እና በባለቤቷ ላይ ሞት መፈረዱን መቋቋም ያቃታት ባለቤቱ በአሁኑ ሰዓት የት እንዳለች እንደማይታወቅ የአስመሮም እህት ሉአም ኃይለስላሴ ተናግራለች፡፡ 

ሉአም እንደምትለው ወንድሟ ከታሰረ ሁለት አመት ሆኖታል፡፡ ጉዳዩም ፑንትላንድ ውስጥ በምትገኘው ቦሳሶ ከተማ ሲታይ ቆይቶ በከተማዋ ያሉ የጎሳ አባላት በሞት እንዲቀጣ ይወስናሉ፡፡ የሞት ቅጣቱ የሚነሳለት ደግሞ 700 ሺህ የኢትዮጵያ ብር ወይም ወደ 40 ሺህ ዶለር አካባቢ ሲከፍል ብቻ እንደሆነ ውሳኔ ያስተላልፋሉ፡፡

ሁኔታው እጅግ ያስጨነቃቸው ቤተሰቦቹ በተለያየ ጊዜ በርካታ ደብዳቤዎችን ለውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት በመፃፍ መንግስት ዲፕሎማሲያዊ ጥረት በማድረግ የወጣቱን ህይወት እንዲያተርፍላቸው ቢማፀኑም ምላሽ ሳያገኙ መቅረታቸውን እህቱ ለአዲስ አድማስ ተናግራለች፡፡

በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያሉ  ጥቅምት 7 ቀን 2004 ዓ.ም ወጣት አስመሮም ቤተሰቦቹን እንዲሰናበት  በማለት አሳሪዎቹ ስልክ ወደ ቤተሰቦቹ እንዲደውል ያደርጋሉ፡፡ በተደወለው ስልክም እስከ አርብ መስከረም 17/2004 ዓ.ም ድረስ ገንዘቡን መክፈል ካልቻለ የሞት ፍርዱ ተፈፃሚ እንደሚሆን ተናግሮ የ “ደህና ሁኑ” መልዕክት  ለቤተሰቦቹ አሰተላልፎ ቤተሰቦቹን ይሰናበታል፡፡

“ ቅጣቱ ፍትሃዊ ባለመሆኑ ተፈጻሚ እንዳይሆን  የቻልነውን ሁሉ ሞከርን፣ የሞት ፍርዱ ሊፈፀም ሁለት ቀናት ብቻ ሲቀሩት የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሠራተኞች ምናልባት በስራ ጫና ወይም ከሱ የባሱ ጉዳዮችን ሲፈፅሙ አቤቱታችንን አልሰሙም ይሆናል በሚል አስበን የመጨረሻ እድል ለመሞከር ጉዳዩን ለሪፖርተር ጋዜጣ አስረዳን እነሱም ዜናውን  ረቡዕ እለት አወጡት፡፡ እስከ ሐሙስ ማታ ድረስ ምንም የተለወጠ ነገር አልነበረም፡፡ ሐሙስ ምሽት ላይ ግን አንድ ስልክ ተደወለልኝ፤ አንድ ሰው ገንዘቡን ከፍሎ የወንድማችሁን ህይወት ሊታደግ ነውና ነገ ትገናኛላችሁ የሚል ነበር” በሚል እህቱ ሁኔታውን ታስረዳለች፡፡

አርብ እለት በደስታና በሲቃ  ተውጣ የተባለው ቦታ ስትደርስ  ገንዘብ ከፍሎ የወጣቱን ህይወት ለመታደግ የወሰነው ግለሰብ አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን ( ቴዲ አፍሮ) መሆኑን ትረዳለች፡፡

“ይህንን ያደረኩት እኔ ሳልሆን እግዚአብሔር ነው፡፡ አይዞሽ ተፅናኚ ብሎ 700 ሺህ ብር የያዘ ቼክ ሰጠኝ፡፡ ማመን አልቻልኩም፡፡ ምን እንደምናገር አላውቅም፡፡ ብቻ በእግዚአብሔርና በቤተሰቦቼ ስም እጅግ አድርጌ አመሰግነዋለሁ” ብላለች፡፡ አክላም “ዱሮም ቢሆን ቴዲን በጣም እወደው ነበር አሁን ደሞ በጣም ወደድኩት” ብላለች፡፡ ገንዘቡን ካገኘች በኋላም ስለ ገንዘቡ አከፋፈልና አስመሮም ከእስር ተለቆ ወደ ሀገሩ ስለሚመለስበት ሁኔታ ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ጋር ቤተሰቦቹ እየተነጋገሩ መሆኑን በመግለፅ ቴዲ አፍሮ የሰጣትን ቼክ መንዝራ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በኩል ገንዘቡ ተከፍሎ ወንድሟ ከእስር እንዲለቀቅ ጥረት በማድረግ ላይ መሆኗን ገልፃለች፡፡

ወጣት አስመሮምን በተመለከተ “ወገናችንን ከሞት እናድን” በሚል ቤተሰቦቹ እና ጓደኞቹ በራሪ ወረቀት ፅፈው በድረ ገፅ የእርዳታ ጥሪያቸውን ሲያሰሙ መቆየታቸውን በመግለፅ “ በመጨረሻ ቴዲ አፍሮ ደረሰልን” ብለዋል ቤተሰቦቹ፡፡

ምንጭ ሳምንታዊው አዲስ አድማስ ጋዜጣ

50 thoughts on “ቴዲ አፍሮ ኢትዮጵያዊውን ወጣት በ700 ሺህ ብር ከሞት አተረፈ

 1. teddy u r always a savior.God bless u and keep the good thing with u.U r always doing good things and u r not greedy and tnx for saving our brother.

 2. eddy,,i am a man so don’t cry very easily but this time u made weep ….
  u are only one and one of your type
  you are supper
  so proud to have country man like you
  may the almighty god be with you and ur family at all times
  “”egiziabeher yitebikeh”””

 3. Tedye men endemeleh alawekem, gen wisteh ende Esate yemined emenet ena ethiopiawinet ale. Egziabher moges yehunew, Emebrehan teketeleh…Yetaserekew yihen melkam neger endetadereg geta asebo bihones. Des yelale

 4. A blessed mind is always blessed! Tedy u are proud to all of us & u r like an angel sent from GOD 4 this man, & Ofcours u r right it is from GOD no one can do things like this by itself specialy in this day but as u said This is from GOD! TEDY GOD bless u more than today!!!

  • This is what expected from one wise person..he is always wise and kind long live for him and this also should be good example for those ”segibgib” habtamoch…

 5. tediye wendime tebarek sira leseriw new ena e/her abizito yibarikih ante ko ye turuye lij bicha aydelehim ye hulum Ethiopian lig neh tebarek lela yemilew yelejim teddi hawei GOD blesssss u

 6. mechem ahunim EGZIABHER alteleyenim. Sadkanin Setonal. Esu yemereteh silehonik enditireda abekah. metadel new. Norot Merdat yalchale ale mikinyatum EGZIABHER yenesun birr letsidk almeretewimina. Teddy EGZIABHER yitebikih.

 7. oh ! tediye min endemil alakim ! bicha Egzabiher ( God) rejimun edmena tena endisetih new yemimegnew hulum kegeta new yemigegnewna geta wiletahin ykfelih . Enwedehalen….

 8. ቴዲ ከነሚስትህ እግዚአብሐር ይባረክህ ጥሩ ኢትዮጵያዊ ልጅ ተባረክ እመቤቴ ትባረክህ ፡፡

What do you say about this? እርስዎ ምን ይላሉ?

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s