Uncategorized

ድንኳን ሰባሪዎች ለሙሽሮች በተዘጋጀ ድግስ ላይ በፈፀሙት ጥቃት ጉዳት ደረሰ

 

ኮተቤ አካባቢ ለሙሽሮች በተዘጋጀ የመልስ ድግስ ላይ በኃይልና በጉልበት “ድንኳን ሰብረው” በገቡ ጎረምሶች በርካታ ተሽከርካሪዎች መሰባበራቸውንና በተጋባዥ እንግዶችም ላይ ጉዳት መድረሱን የሙሽሮቹ የቅርብ ዘመዶች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡ ፖሊስ ጥቃቱ መድረሱን አረጋግጦ፣ ጉዳዩን እየመረመርኩት ነው ብሏል፡፡

በድግሱ ታዳሚዎች ላይ የድንጋይ ውርጅብኝ ያዘነቡት በአካባቢው አስቸጋሪ የሆኑ ጎረምሶች በየካ ክፍለ ከተማ ኮተቤ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን አካባቢ የካቲት 4 ቀን 2004 ዓ.ም. መሆኑን፣ ሙሽሮቹም ትዕግስት ተካና አየናቸው መንግሥቱ እንደሚባሉ ቤተሰቦቻቸው አስታውቀዋል፡፡ ሙሽሮቹ ጋብቻቸውን ጥር 24 ቀን 2004 ዓ.ም. ነበር የፈጸሙት፡፡

ሙሽሪትና ሙሽራው ጋብቻቸውን ከፈጸሙ በኋላ በባህሉ መሠረት “መልስ” ጥሪ መሠረት በሙሽራው እህት ቤት መልስ ተጠርተው ተገኝተዋል፡፡ ከዚያ በፊት ግን ሙሽሪት ትዕግስት ተካና ሙሽራው አየናቸው መንግሥቱ ትልቅ የሠርግ ድግስ ለማድረግ ዕቅድ አልነበራቸውም ተብሏል፡፡

የሙሽራው እህት ወ/ሮ ፍቅርተ መንግሥቱ በነበረው ወግ መሠረት የሙሽሪትንና የሙሽራውን ቤተሰብ ለማቀላቀል ከሠርግ መለስ ያለ ድግስ ያደርጋሉ፡፡ ጥሪው የተደረገውም ባለፈው እሑድ የካቲት 4 ቀን 2004 ዓ.ም. ኮተቤ ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን አካባቢ ከሚገኘው ቤታቸው ነበር፡፡ የተጠራው ግብዣ ግን ባልተጠበቀ የኃይል ጥቃት መደናቀፉን የሙሽራው ወንድም አቶ ኃይለ ማርያም መንግሥቱ ይገልጻሉ፡፡

ሙሽሮች ወደ ግብዣው ቤት ደርሰው በተዘጋጀላቸው ስፍራ ሲደርሱ ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ እንግዶች፣ የአዲስ አበባ ዘመዶችና ጎረቤቶች በድንኳን ሆነው ይጫወታሉ፡፡ ቤቱም በሠርግ ዘፈን ደምቋል፡፡

የተዘጋጀው ማዕድ ተባርኮ የምግብ ማንሳቱ ሥነ ሥርዓት በሙሽሮቹ ይጀመራል፡፡ ሆኖም ታዳሚዎቹ ከማዕዱ ተቋድሰው ሳያበቁ ለድግሱ ያልተጠሩ ግለሰቦች ከውጭ በመግባት ምግብ ማንሳት እንደሚፈልጉ ይገልጻሉ፡፡ በጉልበት ለመግባት የሞከሩም ነበሩ፡፡ የተወሰኑትም ገብተዋል፡፡ የሠርግ ደጋሾች ግጭት እንዳይፈጠር በማለት ከውጭ ሆነው ካልገባን የሚሉትና የገቡትንም ጨምረው ከማዕዱ እንዲያነሱ ማድረጋቸውን ይገልጻሉ፡፡

አቶ ኃይለ ማርያም እንደሚሉት ድንኳን ሰባሪዎቹ ምግብ ከበሉ በኋላ “ጠጅ ካልሰጣችሁን” በሚል ፀብ ይጀምራሉ፡፡ በዚህን ጊዜ ከግቢ እንዲወጡ ይደረጋል፡፡

ከግቢ ቢወጡም ነገር ግን ግቢው ውስጥ እያሉ በውጡ አንወጣም የተጀመረው አለመግባባት ሥር ሰዶ ድንጋይ ውርወራ ይጀመራል፡፡ “የድንጋይ እሩምታ ወረደብን፣ ውጪ የነበሩ ተሽከርካሪዎችም ተሰባበሩ፤” የሚሉት አቶ ኃይለ ማርያም፣ የቤተሰቡ አባላት ራሳቸውን ለመከላከል ጥረት ቢያደርጉም አልተሳካም፡፡ ይልቁንም የድንኳን ሰባሪዎቹ ጉልበት አየለ፡፡ ቁጥራቸውም በዛ፡፡ በዚህም የተነሳ በሰላም የተዘጋጀውና በደስታ ይደመደማል የተባለው ድግስ በሐዘንና በለቅሶ እንዳልሆነ ሆኖ ቀርቷል ሲሉ አቶ ኃይለ ማርያም ሁኔታውን አስረድተዋል፡፡

በመልሱ ድግስ ላይ ደረሰ የተባለውን ያልተጠበቀ ድርጊት በሚመለከት ያነጋገርናቸው የላምበረትና አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል መከላከል ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ሲሳይ ጣሰው፣ “አምባጓሮው ተፈጥሯል፤ በተፈጸመው ድርጊት ላይም ምርመራ እየተካሄደ ነው፤” በማለት በሕግ በተያዘ ጉዳይ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ መስጠት እንደሚያስቸግራቸው ተናግረዋል፡፡

 

ምንጭ ሪፖርተር

Advertisements

What do you say about this? እርስዎ ምን ይላሉ?

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s