East Africa

ኮሚቴ በዛ ውጤት ጠነዛ (በተለይ የወንዶቹ)

By, Befekadu Beyene

 

(በፍቃዱ በየነ) ….እኔን የገረመኝ ግን ምነው የ30ኛው የሎንዶን ኦሎምፒክ የመዝጊያ ስነስርዓት ላይ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ የልዑካን ቡድን አባላት በዙ? እንዴ ያንን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቱታ ለብሰው ሰለሜ ሰሌሜ ሲሉ ላየ እኮ የሰልፉ ርዝመት እና የሚግተለተለው ሰው ብዛት  የጉድ ነበር (መቼም ሰለሜን እንኳን በሰው ሀገር እዚህ ኢትዮጵያ ውስጥም እንደዛ በርከት ያሉ ሰዎች በአንዴ ተጫውተውት አያውቁም፡፡ ለዛውም አንድ አይነት የስፖርት ትጥቅ ለብሰው) እኔማ ቢቸግረኝ ፌደሬሽኑ ቱታችንን እዛ ወስዶ ለሌሎችም ሀገራት አለበሳቸው እንዴ እያልኩ ነበር፡፡ እንደዛ ካልሆነ ታዲያ ያ ሁሉ ሰው ከየት መጣ፡፡

አንዳንድ ጭምጭምታዎች እንደሚያሳዩት ወደ ለንደን የተጓዙት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ኮሚቴ አባላት ብዛት ለውድድር ከቀረቡት አትሌቶች ጋር መሳ ለመሳ ነው፤ አንዳንዶችማ ይበልጣል ሁሉ እያሉ ነው፡፡ የፌደሬሽኖቻችን ነገር አይታወቅም እኮ  “ምናልባት ለአትሌቶቹ ለእያንዳንዳቸው ቦዲ ጋርድ አልያም ደግሞ ደንገጡር ተመድቦ ሊሆን ይችላል”፡፡ በእርግጥ ወርቅና “ሜዳሊያ” ለሚያመጡ እግሮች ለእያንዳንዳቸው ሁለት ሁለት አጣቢ ቢመደብላቸውም አይቆጭም፡፡ . . .ይሁና በቃ ምን አለበት፡፡ ግን ያው ውጤቱ ሁላችንም እንደምናውቀው ነው፡፡ “ኮሚቴ በዛ ውጤት ጠነዛ ( በተለይ የወንዶቹ . . .)”

ሌላው በሳቅ የገደለኝ ነገር …(ማሽላ እያረረ ይስቃል)

የመዝጊያው እለት የወንዶች ማራቶንን ካየሁ በኋላ በጣም በሽቄ ነበር፡፡ በአንድ በኩል በማራቶን ሜዳሊያ ያመጣሉ ተብለው የተጠበቁት አትሌቶች የውኃ ሽታ ሆነው እንደወጡ መቅረት አሳስቦኛል፡፡ ብቻ ተጨማሪ ሜዳሊያ ሲያምረኝ እንደቀረ ኦሎምፒኩም በሰባት ሜዳሊያዎች (ሊያውም በሴቶቻችን ብርታት) እንደተጠናቀቀ ካወቅኩ በኋላ ኦሎምፒክ ቡድኑን ለመደገፍ በ8100 የላክናቸው በርካታ 2 ብሮች ትዝ አሉኝ (ከውጤቱ አንፃር ቆጭቶኝ ሳይሆን አይቀርም፡፡)

ያንን ያእሰብኩ ስብሰለሰል በስልኬ አጭር የፅሁፍ መልዕክት ደረሰኝ፡፡ እንደኔው በሩጫው የተበሳጨ አንዱ ጓደኛዬ አይዞህ ሊለኝ ይሆናል ብዬ የፅሁፍ መልዕክቱን ስከፍተው ባየሁት ነገር ይሄው እስካሁን እየሳቅኩ ነው፡፡ EOC በ8100 የላከው መልዕክት ነበር፡፡ እንዴ ዛሬም ሁለት ብር?! ተወጣ የተባለው 46 ሚሊዮን ብር አነሰ እንዴ? ወገን መተሳሰብ ያለብን አይመስላችሁም? ማለቴ አለ አይደል ብሩ ለታቀደለት አላማ በትክክል መዋል አለመዋሉን . . .

እናንተስ ምን ትላላችሁ ስለ  ዘንድሮው ኦሎምፒክ ውጤታችን እና አሰላለፋችን?

እስኪ  በግልጽ እንወያይ። ሀሳባችሁን ከዚህ ጽሁፍ በታች ባለው ሳጥን ውስጥ ማስቀመጥ ትችላላችሁ።

Advertisements

6 thoughts on “ኮሚቴ በዛ ውጤት ጠነዛ (በተለይ የወንዶቹ)

  1. ትክክል ነው የኔ ወንድም።እንደተባለው የፌዴሬሽኑ ሰዎች በመክፈቻውና በመዝጊያው ላይ በብዛት ተገኝተዋል።ቦርሳቸውንና ልባቸውን አሳብጠው ነገ ከአትሌቶቹ ጋር ይገባሉ።እኔ የአንድ ቀን ስልጣን ቢኖረኝ የመልቀቂያ ደብዳቤ እንዲጽፉ አዛቸው ነበር።

  2. ትክክል ነህ የኔ ወንድም አልተሳሳትክም፡፡ እኔ ስልጣን ቢኖረኝ ሁሉንም ኮሚቴዎች አባርራቸዋለሁ፡፡ ኮሚቴ ቢበዛ ምን ይጠቅማል፡፡ ከብዛት ጥራት፡፡

  3. It is laughable, Ye ethiopian hisb birr manim mecheferiya siyaderg yasazinal,kezih timirt mewused alebin, 8100 yemil machberberia lottery erasachihun tebiku

  4. የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እንደገና እንደአዲስ መዋቀር ያለበት በሙስና የተጨማለቀ ቦታ ነው። ችሎታ ያላቸውን እድሉን ሳይሰጡ ሌላው ከነቤተሰቡ መጓተት ለጉብኝት ነው እንዴ የሄዱት? ወይንስ ለውጤት ይጠና፣ ለአንድ ቀን ስልጣን ቢኖረኝ ከንደገና አዋቅረው ነበር

What do you say about this? እርስዎ ምን ይላሉ?

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s