Uncategorized

ባቡሬ ሆይ. . . .! የእግረኛና የመኪና ማቋረጫችን ወዴት ነው?

addis-ababa-rail-way

By Befekadu Beyene (befekadubt@gmail.com)

ብዙ (ምናልባትም ለሸክም ከሚያዳግተው በላይ) ተስፋ የተጣለበት የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር መንገድ ግንባታ የእግረኛና የመኪና ማቋረጫ ነሽ . . .ወላ አደባባይ ነሽ. . . በብረት ሃዲዶቹ እየቀረደደ ከወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሷል፡፡ ሆ. . . ሆይ…. እሱ ምናለበት ልጄ፡፡ “ወንድድድ የሆነ መኪና በላዬ ላይ አቋርጦ ያልፋል”፤ ያለ ነው የሚመስለው፡፡ በተለይ ከመገናኛ አደባባይ አንስቶ ወደ አያት በሚወስደው መስመር፡፡

እንግዲህ ባቡሬ . . (ተመርቆ ስራ ሲጀምር መዝሙራችን. . .)

“ሸከተፍ ሸከተፍ እያለ ኦሆሆ እሳት እየተፋ

የእገረኛና መኪና ኦሆሆ ማቁዋረጫ አጠፋ . . .” የሚለው እንዳይሆን ስጋት አለ፡፡

ሌሎቹን መስመሮች ትቼ በየቀኑ ሳልፍ ሳገድም በትዝብት የምከታተለውን የመገናኛ ሲኤምሲ መስመር ላንሳ፡፡ በዚህ መስመር ላይ ከጫፍ እስከጫፍ የተዘረጋው የባቡር መንገድ ለጊዜው በብረት ሀዲዱ ላይ በተሞላ ገረጋንቲ ከተሰሩ የመኪና ማቋረጫዎች ውጪ እንድም ዘላቂ ማቋረጫ የለውም፡፡ በቃ ባቡሩ ስራ ሲጀምር መኪኖች ወደ ግራና ቀኝ ማቁዋረጥ ቀርቶ ገልመጥ ብሎ ማየት (ፍሬቻ ማብራት) እንኳን አይችሉም፡፡ አሁን ባለበት ሁኔታ ከቀጠለና ኩባንያው ስራውን አስረክቦ የሚወጣ ከሆነ በዚህ መስመር ያሉ ሌሎች ተሸከርዎች እንደጋሪ ፈረስ ወደፊት ብቻ እያዩ ለመሄድ የሚገደዱ ከሆነ የሚፈጠረውን ችግር አስቡት፡፡

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣንም በተለይ ለእገረኛ ማቁዋረጫ መሰራት አለበት ቢልም ግንባታውን የሚያከናውነው አካል ግን ባቡር ሲመጣ ምልክት የሚሰጠውን መብራት ብቻ እየጠበቁ ማቁዋረጥ ይቻላል የሚል አቁዋም እንዳለው ከሪፖርተር ጋዜጣ ላይ በቅርቡ ማንበባችን አይዘነጋም፡፡

አሁን የሀገሬን ሰው ጠባይ አጥተውት ነው፡፡ አርንጉዋዴ የመንገድ መብራት ምልክት ሲባራ እንኳን በመኪኖች መሃል እየተሹለከለከና እኩል እየተጋፋ መንገድ ለማቁዋረጥ በሚያደርገው ጥረት ስንቱ ለአደጋ እየተጋለጠ መሆኑ ትውስታ እኮ አይደለም: አሁን ዛሬም እየሆነ ያለ ነገር ነው፡፡ በቀለበት መንገዶች ላይ የመሸጋገሪያ ድልድዮች ተገንብተው እንኳን በትራፊክ አደጋ የሚጎዳው እግረኛ ስፍር ቁጥር የለውም፡፡

ከአሁን አሁን እዚህ ጋር መኪና  ማሾለኪያ የሚሆን ድልድይ ነገር ሊገነባ ነው ብለን ብንጠብቅም ግንባታውን እያካሄደ ያለው ኩባንያ ግን ከግራና ከቀኝ የሚያልፉትን መኪኖች ሁላ አይን ዳባ ልበስ ብሎ ግስጋሴውን ቀጥሏል፡፡  ቢያንስ ከአራት አቅጣጫ የሚመጡ መኪኖችን የሚያስተናግዱ አደባባዮችን ለሁለት እየገመሱ ለሀዲዱ ንጣፍ መሬት የሚደለድሉት ዶዘሮችም ወደፊት ሊከሰት ለሚችለው መጨናነቅ “ጆሮችን ጥጥ ነው” ያሉ ይመስላል፡፡

ቢያንስ ከሲኤምሲ ወደመገናኛ መስመር መጥተው በሰአሊተ ምህረት አደባባይ በኩል ወደ ግራ በመታጠፍ ወደ ገርጂ ቦሌ የሚሄዱ መኪኖች የግድ መገናኛ አደባባይ መሄድ ሊኖርባቸው ነው፡፡ ከመገኛኛ ወደ ሲኤምሲ በሚወስደው ረጂም የመኪና መንገድ  ያለው ሁኔታም ወደ ግራ ዞሮ ለመመለስ እጅግ አስቸጋሪና ምናልባትም መዞሪያ ፍለጋ እስከ አያት ድረስ መንዳት የግድ የሚለው ነው፡፡

ይሄ ሊያስከትል የሚችለውን መጨናነቅ እንዲሁም አላስፈላጊ የጊዜና የነዳጅ ወጪ ለመገመት ችግሩ እስኪፈጠር መጠበቅ አያስፈልገውም፡፡ በተለይ አላስፈላጊ የነዳጅና የጊዜ ወጪው በሀገራችን ኢኮኖሚያው እድገት ላይ . . . ብላ ብላ . . . ማለት አልፈልግም፡፡ እሱን ለሀገር ሀሳቢ ኢኮኖሚስቶቹ የቤት ስራ ትቼዋለሁ፤ ካሉ፡፡

ማህንዲስም አይደለሁም፡፡ ያም ቢሆን ግን ከባቡር ሀዲዱ ግራና ቀኝ ወዳሉት መንገዶች የሚያልፉ የእግረኛና የመኪና ማቋረጫዎች ከሌሉ ሊፈጠር የሚችለውን ችግር ከወዲሁ ለመገመት አያዳግተኝም፡፡

ነው ወይስ ባቡሩ ስራ ሲጀምር የግልና የቤት መኪናዎች ታክሲዎችና የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች ሁላ ስራ እንደሚያቆሙ ታስቧል?

እኔ እስከማውቀው ድረስ ባቡሩ የአዲስ አበባችንን የትራንስፖርት አገልግሎት ለማገዝ እንጂ ሁሉንም አዲስ አበቤ ጠቅልሎ ለማጋዝ አይደለም እየተሰራ ያለው፡፡

አሁንም እላለሁ ባቡሬ ሆይ እባክህ ከእግሮችህ ብረት ስር መኪኖች የሚያልፉበትን ቀዳዳ ክፈት፡፡  በሚያመችህ በኩልም ለእግረኛ አዲስ አበቤዎች መሻገሪያ አስብላቸው፡፡

 

Read More from Ethiopian Observer . . .

Young Ethiopians Support Themselves Through Condom Distribution

Mobiles to Give Sexual and Reproductive Health Information to Young People

ሀይቅን ለእነ ባህር ዳር ብቻ ማን ሰጣቸው? አዲስ አበባም ሀይቅ አላት

“ለመጀመሪያ ጊዜ በባዶ እግሩ የሮጠው ሰው”?

ስንት ሰው ባዶ እግሩን በሚዳክርባት ሀገር ስለ ሩኒ ጫማ አውልቆ በካልሲ መሄድ ማውራት ስድብ አይደለምን

የ40/60 ወር አዲስ አበባን መቶ በመቶ ሲያምሳት ከረመ

 

Open-air classes in Ethiopia teach rural women about family planning and HIV

Advertisements

What do you say about this? እርስዎ ምን ይላሉ?

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s