Uncategorized

እናኑ አለሙ ከሶስት አስርት አመታት በላይ በድጋፍ ማጣት ውስጥ የተደበቀችው ሰዓሊ

Enanu & some of her works

Enanu & some of her works

የስዕል ስራዎቹዋ በአብዛኛው ሴቶች ላይ ያተኮሩ ናቸው፡፡ ሴቶች ያለባቸውን የስራ ጫና እና ስራ ፍለጋ ከገጠር ወደ ከተማ የሚያደርጉትን ፍልሰት  እንዲሁም  የተለያዩ የሴቶች ባህላዊ አለባበሶችን የሚያሳዩ ስእሎች ከስራዎቹዋ መካከል ይጠቀሳሉ፡፡ መምህርት እና የስነ ጥበብ ሰው እናኑ ዓለሙ፡፡

ከህፃንነቱዋ ጀምሮ ስሜቶቿን በስዕል የመግለፅ ልምድ የነበራት እናኑ የሪያሊስቲክ አሳሳል ዘይቤን ነው የምትከተለው፡፡

በተለይ የአርቲስት ደስታ ገብሩ አድናቂ ናት:: “አርቲስት ደስታ ገብሩ ለሁለም ሰው አርአያ መሆን የምትችል ብዙ ክብርና ሞገስ ልሰጣት የምችል ሰው ነች፡፡”  ትላለች፡፡

የአምስት ልጆች እናት የሆነችው አንጋፋ የስነ ጥበበው ሰው ህይወት ሴቶች ህልማቸውን ለማሳካትና በሙያቸው ለመግፋት ምን ያህል ፈተናዎች አንደሚያጋጥሙዋቸው ይናገራል፡፡

እናኑን ስዕል ለስእር ዳርጓታል፡ ከእስርም አስፈትታል

አዲስ አበባ ስነጥበባት ትምህርት ቤት ተማሪ የነበረቸበት ዘመን የአቢዮት ወቅት በመሆኑ ኢህአፓዎች የተለያዩ የቅስቀሳ ህትመቶችን የሚበትኑበት ወቅት ነበር፡፡ ወጣቷ እናኑ ደግሞ ቀለም ከእጇ አይለይም፡፡ ልብሶቿም ከህብረ ቀለማት ጠብታዎች ፀድተው አያውቁም፡፡ በዚህም ምክንያት ከኢሕአፓ ፅሁፎች ጋር በተያያዘ ተጠርጥራ ለስድስት ወር ታሰረች፡፡ ልትመረቅ ትንሽ ሲቀራት በመታሰሯ የተበሳጨችው እናኑ በታሰረችበት ከፍተኛ 34 አስር ቤት ውስጥ ተስፋ መቁረጥ ጀምራ እንደነበር ትናገራለች፡፡

Women are always at the center of Enanu's paintings

Women are always at the center of Enanu’s paintings

«ቤተሰቦቼ አነስተኛ ገቢ ያላቸው እና እራሳቸውን ረድተው የሚኖረ ስለነበሩ፡ ቶሎ ተመርቄ ስራ ይዤ መርዳት እፍልግ ነበር፡፡ ሆኖም ግን ልመረቅ ስድስት ወር ሲቀረኝ ስለታሰርኩኝ በብስጭት በቃ ብሞትም ምንም አይመስለኝም ነበር፡፡»

በተስፋ መቁረጡዋ ምክንያት ከሌሎቹ እስረኞች ያፈነገጠ ባህሪ ማሳየቷን ያስተዋለው የእስር ቤቱ አዛዥ እናኑን ቢሮው ያስጠራታል፡፡

አዛዡ  ስለትምህርቷ ሁኔታ ሲጠይቃት በድፍረት “እናንተ እስካሰራችሁኝ ሰዓት ጊዜ ድረስ እማር ነበር፡፡የምማረው  የስነጥበብ ትምህርት ነበር፡፡ ቤቴ ቀለም ስለተገኘብኝ በጥርጣሬ ነው የታሰርኩት፡፡ ትምህርቴን ያቋረጥኩት በእናንተ ምክንያት ነው” የሚል መልስ ሰጠችው፡፡

አዛዡም የምትለውን ለማረጋገጥ ወረቀትና እስኪርቢቶ ሰጥቶ ስለላብ አደሩ አስኪ ሳይልኝ የሚል ፈተና ያቀርብላታል፡፡ እዛው ቢሮው ቁጭ ብላ በሰራችው ንድፍ የተደነቀው አዛዥ አሁን ወደ ቤትሽ ሂጂ ነገር ግን በየሳምንቱ ሀሙስ ሀሙስ የእስረኞች ቁጥጥር ስለሚካሄድ ተመልሰሽ ትመጫለሽ ብሎ በራሱ መኪና ቤቷ አደረሳት፡፡

ብዙ ጓደኞቹዋ ለረጂም አመታት እንደታሰሩ የተገደሉም እንዳሉ እና እሷ በስዕል ምክንያት መፈታቷን ስታስበው እድለኛ እንደሆነች ይሰማታል፡፡

ወደ ስነጥበባት ትምርት ቤት ስትመለስ በእስር በነበረችባቸው ስድስት ወራት ያለፏትን ስራዎች ሁሉ ሌት ከቀን ሰርታ በማጠናቀቅ ከክፍል ጓደኞቿ ጋር በ1970 ዓ.ም ተመረቀች፡፡

ከካሳንቺስ እስከ ጎንደር ደባርቅ እና ደብረብርሃን

እናኑ አዲስ አበባ ሂልተን ሆቴል አካባቢ ተወልዳ ካዛንቺስ ነው ያደገችው፡፡ እስከ ዘጠነኛ ክፍል ድረስ ያለውን ትምህርቷን በግርማዊት እቴጌ መነን ተከታትላለች፡፡  ዘጠነኛ ከፍልን እንዳጠናቀቀች ያመራችው ግን ወደ አዲስ አበባ ስነጥበባት ትምህርት ቤት ነበር፡፡ በ1966 ዓ.ም፡፡

ለአምስት አመታት ያህል በግራፊክስ ትምህርት ክፍል ተምራ ስተመረቅ በወቅቱ ከኮሌጅ እንደተመረቁ ማስተማር ግዴታ ስለነበር በወጣላት እጣ መሰረት ወደ ሰሜን ጎንደር ደባርቅ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አቀናች፡፡ ለስድስት አመታት ካስተማረች በኋዋላም በ1977 ዓ.ም ወደ ደብረ ብርሃን ተዛወረች፡፡

ብሩህ ተስፋ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ብሉ ምኒል ኮሌጅ . . . በሁዋላም ደብረብርሃን ትምህርትና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ በስነጥበብ መምህረነት አገልግላለች፡፡ ከማስተማር ጎን ለጎን በትምህርት ማበልፀጊያ ማዕከላት የተለያዩ የትምህርት አጋዥ መሳሪዎችንም ታዘጋጅ ነበር፡፡በግሉዋ የስነጥበብ ማስተማሪያ ማኑዋል አዘጋጅታ ለተለያዩ ትምህርት ቤቶች አበርክታለች፡፡ የስእል ስራዎቿንም አላቋረጠችም፡፡

ምኞት አቅም ማጣትና የሴትነት ፈተናዎች

ስራዎቿን አውጥታ በኤግዚቢሽን መልክ ማሳየት መቻል የእናኑ የሁል ጊዜም ምኞት ነው፡፡ ነገር ግን በአቅም ማነስና በአጋዥ ማጣት ምክንያት እስካሁን ህልሟ ተሳክቶ ማየት አልቻለችም፡፡ ከሶስት አስርት አመታት በላይ በስእል ህይወት ውስጥ ለቆየችው የጥበብ ሰው ይሄ ከምንም በላይ የሚያስቆጫት ነገር ነው፡፡

“የልጆች እናት ስለሆንኩም የሚረዳኝ ሰው ባለመኖሩ ስራዎቼን ማቅረብ አልቻልኩም፡፡ የሚቆጨኝ ነገር ቢኖር መስራት እየቻልኩ  ስራዎቼን ማቅረብ አለመቻሌ ነው፡፡”

በትዳር ህይወት ወስጥ በባለቤቱዋ ከፍተኛ ጫና ይደረግባት እንደነበር የምትገልፀው እናኑ በዚህም ምክንያት ብዙ ችግሮች እንዳጋጠሙዋት ገልፃልኛለች፡፡

“ባለቤቴ ከቤት እንድወጣ አይፈልግም ነበር፡፡ በሙያዬ ተፈልጌ ሄጄ በምሰራበት ወቅት ከቤት ተቃዉሞ ይገጥመኝ ነበር፡፡ እሱንም ችዬ ስሰራ ነበር፡፡ መጨረሻ ላይ ልቋቋመው ስላልቻልኩ (ትዳሬን) ትቼ ወጥቻለሁ፡፡”

ስራዎቿ ለምን በብዛት ሴቶች ላይ እንደሚያተኩሩ ለጠየቀ ሰው አሁን ምላሹ ግልፅ መሆኑ አያጠራጥርም፡፡

እናኑ አሁንም  ብሩሽ ከእጇ አልተለየም

ምንም አንዃን የህይወት ውጣ ውረድና የሚገጥማት ፈተና ስራዎቿን ለህዝብ ከማድረስ ቢያግዳትም እናኑ አሁንም ስእል ከመሳል አትቦዝንም፡፡ ከቤት ማፅዳት፣ ምግብ ማብሰልና ከስራ መልስ በምታገኘው ትርፍ ጊዜ እራሷን ከቀለማት መሀል ማግኘት ያስደስታታል፡፡ ቤቱዋን ውስጥ በቅርብ ጊዜ የሳለቻቸው በርካታ የስእል ስራዎች አሉ፡፡ ቀደምት  ስራዎቿ በጉዋደኞቿ እጅ፣ በሰራችባቸዉ ተቋማት እና የተለያዩ ቦታዎች ይኛሉ፡፡

“ስዕል ቋንቋዬ ነው ለኔ፡፡ ብዙ ማውራት ሳይጠበቅብህ በአንዲት ትንሽ ስእል ከሺህ በላይ ቃላትን መመንዘር ያስችላል” ትላለች የ 59 አመት አድሜዋ እናኑ፡፡ አሁንም የሚያግዛት ብታገኝ ለህዝብ የሚደርሱ ስራዎችን መስራት እንደምትችል በመተማመን፡፡

ለሙያዋ ያላትን ፍቅር፣ በእራስ የመተማመን መንፈሷንና ፅናቷን ላዬ ሴቶች ምን ያህል ጠንካራ እንደሆኑ መገንዘብ አያዳግተውም፡፡

መምህርና የስነ ጥበብ ሰው እናኑ ዓለሙ፣ የእሷ አይነት ሴቶች ህይወት የሚገባቸው እና ጥበብ አፍቃሪያን የሆኑ ሁሉ ከጎኗ ሊቆሙላት የሚገባት ሴት፡፡

በፍቃዱ በየነ (www. ethiopianobserver.wordpress.com)

====//====

መምህርና የስነ ጥበብ ሰው እናኑ ዓለሙን  ማግኘት እና ማገዝ የምትፈልጉ የዚህን አጭር ታሪክ ፀሃፊ በተከታዩ ኢሜይል ማግኘት ትችላላችሁ፡፡  lambadena@gmail.com

Advertisements

What do you say about this? እርስዎ ምን ይላሉ?

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s